Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚያካሂደውን ሕዝበ ውሣኔ ለማስፈጸም የተመለመሉ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎችን ለሚያሠለጥኑ የመሥክ አሠልጣኞች ኅዳር 27-29 ቀን 2015 ዓ.ም. ሥልጠና ሰጠ

በቦርዱ የስልጠና ስራ ክፍል ለ299 የመሥክ አሠልጣኞች በሁለት ዙር የተሰጠው ሥልጠና በአርባ ምንጭ ከተማ የተካሄደ ሲሆን፤ ሥልጠናውም በሕዝበ ውሣኔው የመራጮች ምዝገባ ሂደት የተለያዩ ደረጃዎች ላይ የሚከናወኑ ተግባራትና ጥቅም ላይ የሚውሉ ቁሳቁሶችን የተመለከተ የንደፈ ሃሳብና የተግባር ልምምድ አካቷል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ለሚያካሂደው ሕዝበ ውሳኔ በተለያየ የኃላፊነት ደረጃ ላይ ለሚሠማሩ አስተባባሪዎቹ ሥልጠና ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ለሚያካሂደው ሕዝበ ውሳኔ በተለያየ የኃላፊነት ደረጃ በሕዝበ ውሣኔው የዞን/ልዩ ወረዳ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች እና ማስተባበሪያ ማእከላት ለሚሠማሩ አስተባባሪዎቹ ኅዳር 21 እና 22 ቀን 2015 ዓ.ም. በሁለት ዙር ሥልጠና ሰጠ።

Share this post

የሕዝበ ውሳኔው ጥያቄ እና ምልክቶች ስለማሳወቅ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ቱ ዞኖች (ኮንሶ፣ ወላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና በ5ቱ ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ህዝበ ውሳኔ ለማካሄድ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል። በዚሁ መሰረት ቦርዱ የህዝበ ውሳኔ ጥያቄ በተመለከተ ውሣኔ ሰጥቷል፡፡ ምልክቶችን የማስመረጥም ሂደት አከናውኗል፡፡

የሕዝበ ውሣኔው ጥያቄ አማራጮች፡-

1. “የ6ቱ ዞኖች (ኮንሶ፣ ወላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና 5ቱ ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) በአንድ የጋራ ክልል መደራጀትን እደግፋለሁ” የሚለው ነው፡፡ ለዚህ ጥያቄ ምልክት ነጭ እርግብ በአስተዳደር ምክር ቤቶቹ ተመርጧል፡፡

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ እነአቶ ዘለሌ ጸጋሥላሴ (19 ሰዎች) ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲን አስመልክቶ ያቀረቡትን የተለያዩ ቅሬታዎች ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ መርምሯል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ እነአቶ ዘለሌ ጸጋሥላሴ (19 ሰዎች) ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲን አስመልክቶ ያቀረቡትን የተለያዩ ቅሬታዎች ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በነሐሴ 15 ቀን 2014 ዓ.ም. አቶ አምሀ ዳኜው ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ ያሣለፈውን ውሣኔና በተመለከተ የተሰጠ ማብራሪያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት በነሐሴ 15 ቀን 2014 ዓ.ም. ለሦስተኛ ጊዜ ተጠርቶ አቶ አምሀ ዳኜው ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ ያሣለፈውን ውሣኔና ጠቅላላ ጉባዔ ለመጥራት የሄደበት ሂደት አስመልክቶ ፓርቲው ያቀረበውን ሠነድ ከዐዋጁና ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ አንጻር በመመርመር ሂደቱ የተሟላ በመሆኑ ቦርዱ ተቀብሎታል። በመሆኑም ፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔውን የሚያካሂድበትን ቀን በመቁረጥ ለቦርዱ በማሳወቅ እንዲያከናውን ቦርዱ ወሥኗል።

ደብዳቤው እዚህ ላይ ያገኙታል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች ላይ ለሚያካሂደው ሕዝበ ውሣኔ የተፈፀሙ ዋና ተግባራት

የዕቅድና በጀት ዝግጅት

  • ህዝበ ውሣኔውን የሚካሄድባቸውን ቦታዎች እና ምርጫ ጣቢያዎችን በመለየት፣ መረጃዎችን በማሰባሰብ እና በማደራጀት ቦርዱ ዝርዝር ዕቅድ አዘጋጅቶ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አቅርቧል። (መስከረም 10 ቀን 2015 ዓ.ም)
  • የህዝበ ውሳኔውን ለማስፈጸም ከተጠየቀው በጀት ብር 541 ,270,104.82 (አምስት መቶ አርባ አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰባ ሺ አንድ መቶ አራት ብር ከሰማኒያ ሁለት ሳንቲም) ውስጥ 410,100,000 (አራት መቶ አስር ሚሊዮን አንድ መቶ ሺ) ተፈቅዶ ወደ ሥራ ተገብቷል። (ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ/ም)
  • በቀጣይም ተጨማሪ በጀት የሚያስፈልጋቸውን ዝርዝር ተግባራት አዘጋጅቶ ያቀርባል።

የህዝበ ውሳኔ ጽ/ቤቶችን ማደራጀት

Share this post

የቡሌ ምርጫ ክልል የድጋሚ ምርጫን በተመለከተ የተሰጠ ውሣኔ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. እና መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም. በሁለት ዙር ማከናወኑ ይታወቃል። ቦርዱ በተያዘው በጀት ዓመት በተለያዩ ምክንያቶች 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ባልተካሄዱባቸው የተወሠኑ የምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫ ለማከናወን የቅድመ ዝግጅቶች ሥራዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል።

ቀደም ሲል ቦርዱ 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ካካሄደባቸው ምርጫ ክልሎች አንዱ በሆነው በቡሌ ምርጫ ክልል የተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ላይ መጠነ ሰፊ የሕግ ጥሰት እንደነበር በማረጋገጡ ምርጫው በድጋሚ እንዲከናወን ጥቅምት 19 ቀን 2014 ዓ.ም. መወሠኑ ይታወቃል። ይህንንም የድጋሜ ምርጫ በተያዘው ዓመት በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ከሚካሄደው ሕዝበ ውሣኔ ጋር በአንድ መርኅ ግብር ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. አብሮ እንዲከናወን ቦርዱ ኅዳር 03 ቀን 2015 ዓ.ም. ወሥኗል።

Share this post

ማስታወቂያ: በምርጫ አስፈጻሚነት መሣተፍ ለሚፈልጉ አመልካቾች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደ/ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ለሚያካሄደው ሕዝብ ውሣኔ፤ በምርጫ አስፈጻሚነት ለመሣተፍ ፍላጎት ያላቸውን አመልካቾች ማስታወቂያ በማውጣት መመዝገቡ ይታወቃል። ሆኖም ሕዝበ ውሣኔው በሚካሄድባቸው የተወሠኑ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ውስጥ ባሉ ቀበሌዎች እና ምርጫ ጣቢያዎች ላይ በቂ ምርጫ አስፈጻሚ ባለመገኘቱ ፍላጎት ያላቹ አመልካቾች እስከ ኅዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ በመጫን እንድታመለክቱ ቦርዱ ያሳውቃል።

ለማመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ

ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ ዐዋጅ ቁጥር 1133/2011 እና በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሠረት የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመመዝገብ ኃላፊነት ተሰጥቶታል።

በዚሁ መሠረት በእነአቶ ዩሱፍ ሁሴን “የሱማሌ ፌዴራሊስት ፓርቲ (ሱ.ፌ.ፓ)” በሚል ስያሜ የክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባ ጥያቄ ያቀረቡ በመሆኑ በዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 68 ንዑስ አንቀጽ ሁለት እና ሦስት መሠረት በፓርቲው ስም፣ ዐርማ ወይም ሌሎች ጉዳዮች ተቃውሞ ያለው ሰው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከዛሬ ኅዳር 8 ቀን 2015 ዓ. ም. ጀምሮ በ14 ቀናት ውስጥ ተቃውሞውን የቦርዱ ዋናው መሥሪያ ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 207 እንዲያቀርብ ቦርዱ ያሳስባል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ