Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል የሚካሄደውን ሕዝበ ውሣኔ በተመለከተ ከአስተዳደር እና ጸጥታ አካላት ጋር ምክክር አካሄደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙት የጋሞ፣ ጎፋ፣ ወላይታ፣ ጌዲዮ፣ ኮንሶና፣ ደቡብ ኦሞ ዞኖች እንዲሁም የቡርጂ፣ አማሮ፣ ደራሼ፣ ባስኬቶ እና አሌ ልዩ ወረዳዎች የሚያካሄደውን ሕዝበ ውሣኔ በተመለከተ ጥቅምት 7 ቀን 2015 ዓ.ም ከአስተዳደር እና ጸጥታ አካለት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡

በምክክር መድረኩ የሕዝብ ውሣኔው አጠቃላይ ዕቅድና አፈጻጸሙን በተመለከተ ገለጻ ተደርጓል። የህዝበ ውሳኔውን ሰላማዊነት ከማረጋጋጥ እና ከሎጅስቲክስ አንፃር የክልሉ እና የአካባቢ አስተዳደር መዋቅሮች ያለባቸው ሀላፊነት በተመለከተም ማብራሪያ ተሰጥቷል።

Share this post

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መካከል የጋራ ስምምነት ሠነድ (Memorandum of Understanding) ተፈረመ

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ እና በጋራ ምክር ቤቱ ዋና ሰብሳቢ መብራቱ አለሙ (ዶ/ር) አማካኝነት ዛሬ ጥቅምት 9 ቀን 2015 ዓ.ም. የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሠነድ ምክር ቤቱ መጋቢት 2011 ዓ.ም በፓርቲዎች መካከል የተፈረመውን የቃል ኪዳን ሠነድ ዐላማ ለማሳካት ለሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ቦርዱ ድጋፍ ለማድረግ ይችል ዘንድ፤ እንዲሁም ምክር ቤቱም የሚሰጠውን ድጋፍ በመግባቢያ ሠነዱ ውስጥ በተጣለበት ኃላፊነት መሠረት ለታለመለት ዐላማ ማዋሉን ለማረጋገጥ የተፈረመ ነው፡፡

በዚህ የመግባቢያ ስምምነት መሠረት ቦርዱ ለምክር ቤቱ ድጋፍ ከሚያደርግባቸውና ከምክር ቤቱ ጋር የጋራ መግባባት ከተደረሰባቸው ውስጥ : -

• የምክር ቤቱ ገጽታ ግንባታ ስራዎች (ለመጽሔት ዝግጅት፤ ለማስታወቂያና ተዛማጅ ስራዎች )

• ፕሬስ ኮንፈረንስ ማዘጋጀት፣

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል የሚካሄደውን ሕዝበ ውሣኔ በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥቅምት 1 እና 2 ቀን 2015 ዓ.ም. በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ የጋሞ፣ ጎፋ፣ ወላይታ፣ ጌዲዮ፣ኮንሶና፣ደቡብ ኦሞ ዞኖች እንዲሁም የቡርጂ፣አማሮ፣ደራሼ፣ባስኬቶ፣አሌ ልዩ ወረዳዎች የሚካሄደውን ሕዝበ ውሣኔ በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄዷል። የመድረኩ ዐላማ የሕዝበ ውሣኔው አጠቃላይ ዕቅድና የዝግጅት መለኪያዎች፣ የሕዝበ ውሣኔው አደረጃጀት፣ እያንዳንዱን የታቀዱ ተግባራት ለመፈጸም የሚያስፈልገው የጊዜ ሁኔታ፣ ከአስተዳደር አካላትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚጠበቁ ኃላፊነቶችን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመመካከርና ተጨማሪ ግብዓት በመውሰድ የመጨረሻውን የጊዜ ሠሌዳ ማዘጋጀት እንደሆነ ተጠቅሷል ፡፡

Share this post

የአጭር ጊዜ ሥራ ቅጥር ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ላይ ከተመዘገቡት የመራጮች መዝገብ መረጃ ውስጥ በሙከራ ደረጃ ወደ መረጃ ቋት የማስገባት ሥራ (pilot Voters List Digitization and Auditing) ለማሠራት ባቀደው መሠረት ሥራውን ለማከናወን የሚችሉ ብቃት ያላቸውን ባለሞያዎች መልምሎ ለአጭር ጊዜ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም መረጃን ወደ መረጃ ቋት የማስገባት (Data Encoding) የሥራ ልምድ ያላቸሁ፡-

1. በማንኛውም የትምህርት ዘርፍ ቢያንስ በድግሪ የተመረቃችሁ

2. ቢያንስ የአንድ ዓመት የሥራ ልምድ (በተለይ በዳታ ማስገባት (Data encoding) ላይ ልምድ ያላቸው ቢሆን ይመረጣል)

3. የሥራ ቋንቋውን አቀላጥፈው ማንበብና መፃፍ የሚችሉ

4. ሴቶች አመልካቾች የሥራ ልምዱ ካላቸውና ሌሎች መስፈርቶችን የሚያሟሉ ከሆነ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።

የሕዝበ ውሣኔ የትግበራ አፈጻጸም ዝርዝር ዕቅድ ማሳያ ረቂቅ የጊዜ ሠሌዳ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ የሚያካሄደው ሕዝበ ውሣኔ የትግበራ አፈጻጸም ዝርዝር ዕቅድ ማሳያ ረቂቅ የጊዜ ሠሌዳ. የጊዜ ሰሌዳዉ ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ

ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 100 ንዑስ አንቀጽ 2 በተሰጠው ስልጣን መሠረት መንግስት ለፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ለመወሰን መመሪያ በማውጣትና በስራ ላይ በማዋል ለ2014 በጀት ዓመት የተፈቀደውን ድጋፍ በመስፈርቱ መሠረት አከፋፍሎ ለፖለቲካ ፓርቲዎች በከፈቱት የተለየ የባንክ ሂሣብ ቁጥር ገቢ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም በ2014 በጀት ዓመት በመስፈርቱ መሠረት በባንክ ሂሣብ ቁጥራችሁ ገቢ የሆነውን የፋይናንስ ድጋፍ በአዋጁ አንቀፅ 82 መሠረት በተመሰከረለት የውጭ ኦዲተር በማስመርመር እስከ ኅዳር 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ለቦርዱ ሪፖርት እንድታቀርቡ ያሳውቃል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከኬንያ የምርጫ ኮሚሽን (Independent Electoral and Boundaries Commission (IEBC)) እና ከኬንያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሬጂስትራር ቢሮ (Office of the Registrar of Political Parties) አመራሮች ጋር የልምድ ልውውጥ አደረገ

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ እና በምክትል ሰብሳቢው ውብሸት አየለ የተመራ ልዑክ ከኬንያ የምርጫ ኮሚሽን እና ከኬንያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሬጂስትራር ቢሮ አመራሮች ጋር የልምድ ልውውጥ አደረገ። በልምድ ልውውጥ ላይ የቦርዱ የኦፕሬሽን፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች እና በተለያዩ ኃላፊነት የሚሠሩ የቦርዱ ባልደረቦች እየተሣተፉ ይገኛሉ።

በዚህ የሁለትዮሽ የልምድ ልውውጥ ላይ ከዋነኛ የምርጫ ሂደቶች ውስጥ ከሚካተቱት፤ እንደ የምርጫ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ የመራጮች ምዝገባ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ፣ እንዲሁም የአስተዳደር እና የፋይናንስ ጉዳዮችን የተመለከቱ አሠራሮችን እና ልምዶችን ለመለዋወጥ ተችሏል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን አስመልክቶ እያስጠና ያለው ጥናት ላይ ውይይት አካሄደ

መስከረም 19 ቀን 2015 ዓ.ም. የባለድርሻ አካላትን ምክረ-ሃሳብ ለመሰብሰብ ታስቦ የተዘጋጀውን መድረክ በንግግር የከፈቱት የቦርድ አመራር አባል የሆኑት ብዙወርቅ ከተተ ሲሆኑ፤ በንግግርቸውም ጥናቱን ያከናወኑትን ባለሞያዎችንና የመድረኩ ተሣታፊዎች አመስግነው፤ ከመድረኩ የሚገኙት አስተያየቶች ጥናቱን በተሻለ ለማዳበር ወሣኝ ከመሆኑም ባሻገር ቦርዱ በቀጣይ ለሚያካሂዳቸው ምርጫዎች ትልቅ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው ገልጸዋል። አክለውም ጥናቱ በምርጫ ቦርድ ታሪክ ምናልባትም በዓይነቱ የመጀመሪያ ሊባል የሚችል ነው ብለዋል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ መስከረም 29 ቀን 2015 ዓ. ም. አካሂደዋለሁ ያለውን ጠቅላላ ጉባዔ አስመልክቶ የሰጠዉ ምላሽ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ መስከረም 29 ቀን 2015 ዓ. ም. አካሂደዋለሁ ያለውን ጠቅላላ ጉባዔ አስመልክቶ ያስገባውን ሠነድ መርምሮ ሕጉንና የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብ የተከተለ ሆኖ ስላላገኘው ውድቅ አድርጎታል።

የውሣኔውን ሙሉ ዝርዝር እዚህ ላይ ያገኙታል

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ). ሰኔ 25 እና 26 ቀን 2014 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ በተመለከተ በቀረቡለት አቤቱታዎች ላይ ተከታዮቹን ውሣኔዎች አስተላልፏል

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ አባል የሆኑት እነአቶ ዘመኑ ሞላ (ስድስት ሰዎች) ነሐሴ 16 ቀን 2014 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት አቤቱታ ፓርቲው ሰኔ 25 እና 26 ቀን 2014 ዓ.ም. ባከናወነው 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የተለያዩ የደንብ ጥሠቶች ተፈጽመዋል በማለት ለቦርዱ ሰኔ 21 እና 29 እንዲሁም ሐምሌ 5 ቀን 2014 ዓ.ም. ያቀረቡትን አቤቱታ ለማጠናከር ይረዳል ያሉትን ተጨማሪ ማስረጃዎችን አቅርበዋል። በሌላ በኩል እነአቶ ደሳለኝ በዛብህ (ሁለት ሰዎች) እንዲሁ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ ተመሳሳይ አየቱታ አቅርበዋል፡፡

Share this post