1. የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1133/2011

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህገ መንግሥቱ ላይ የተቀመጠውን መሠረት በማድረግ በአዋጅ የተቋቋመ ተቋም ሲሆን ማቋቋሚያ ህጉም “የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1133/2011” ተብሎ ይጠራል፡፡ አዋጁ የተሻሻለው የኢትዮጵያ ምርጫ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ላይ የነበሩ የምርጫ አስፈጻሚ ተቋሙን አመሰራረትና ኃላፊነቶች ድንጋጌዎችን በመሻር መጋቢት 23 ቀን 2011 ዓ.ም. ፀድቆ ሥራ ላይ ውሏል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ የተሻሻለበት ዓላማ የዜጎችን እራስን በራስ የማስተዳደር መብት ከማንኛውም አካል ነፃ በሆነ የምርጫ አስፈፃሚ ተቋም እንዲመራ፤ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባላትን አመላመልና አሿሿም ግልጽ ለማድረግ እና በተወዳዳሪ ድርጅቶች እና በመራጮች ዘንድ ያለውን ተአማኒነት እና የማስፈጸም አቅም ለማሳደግ እንዲረዳ ነው፡፡ የማቋቋሚያ አዋጁ ስለቦርዱ ሥልጣንና ተግባር፣ ስለቦርድ አባላት አሰያየም እና ሥነ ምግባር የሚደነግጉ ዝርዝር ክፍሎችን ይዟል፡፡

አዋጅ ቁጥር 1133/2011 ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ (PDFየብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ)

2. የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011

ምርጫን ፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባን እና ተያያዥ ሥነ ምግባርን የሚገዛው ግ “የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011” ተብሎ ይጠራል፡፡ አዋጁ ስት ቀደም ሲል የነበሩ የተለያዩ ህጎችን ማለትም የኢትዮጵያ የምርጫ ህግ አዋጅ ቁጥር 532/1999፣ የተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2000 እና የፓለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 662/2002 በመሻር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነሐሴ 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ፀድቆ ሥራ ላይ ውሏል፡፡

የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ የተሻሻለበት ላማ ምርጫ ሁሉን አቀፍ፣ ነፃ ፍትሃዊና ሰላማዊ እንዲሆን ለማድረግ፣ የለም አቀፍ የምርጫ መርሆችን አካቶ እንዲይዝ ለማስቻል፣ ዜጎች በቀጥታና በነፃነት በመረጧቸው ተወካዮች እራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር ስልጣናቸውን በተግባር ላይ ለማዋል፣ ፓለቲካ ፓርቲዎች የፓርቲ ፕሮግራምና ላማቸውን ማራመድ እንዲችሉ፣ ዜጎችና ፓርቲዎች በምርጫ ርዓት ውስጥ የሚኖራቸውን መብትና ግዴታ ለመደንገግ እና ለምርጫ ሂደት ለሚነሱ አለመግባባቶች አስተዳደራዊ እና የዳኝነት መፍትሄ የሚሰጡ ተቋማትን እና አሰራራቸውን ለመወሰን ነው፡፡ የምርጫ ህጉ በዋናነት ስለ ምርጫ ደንብና መርህ፣ ስለፓለቲካ ፓርቲዎች፣ ስለምርጫ ታዛቢዎችና የመራጮች ትምህርት አሰጣጥ፤ በምርጫ ስለሚነሱ አቤቱታዎች እና ክርክሮች እና ስለምርጫ ሥነ ምግባር የሚተነትኑ ዋና ዋና ክፍሎችን ይዟል፡፡

አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ (PDF የኢትዮጵያ የምርጫ፥ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ 1162)

3. በአዲሱ የምርጫ የፖለቲካ ምዝገባ እና የሥነ ምግባር ህግ የተለወጡ ዋና ዋና ጉዳዮች

በአዲሱ የምርጫ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የሥነ ምግባር ህግ ከቀድሞው ህግ በተለየ መሠረታዊ የሆኑ እና ቅሬታ ሲቀርብባቸው የነበሩ ጉዳዮች ላይ ማሻሻያ አድርጓል፡፡ በዚህም መሠረት በህጉ ላይ የተቀየሩትን ዋና ዋና ይዘቶች ለማየት ከስር የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ  በመጫን ይመልከቱ (PDFበረቂቅ አዋጁ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሚመለከተው ክፍል ከተካተቱት አዳዲስ ጉዳዮች ዋናዎቹ)

4. ደንቦችና የቃልኪዳን ሰነዶች

PDF    የምርጫ ቁሳቁስ እና ሰነዶች ርክክብ እና የማስወገድ ሂደት መመሪያ

PDF    በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚኖረውን ግንኙነት እንዲሁም በተናጠል የሚያደርጓቸውን እንቅስቃሴዎች የሚገዛ የአሠራር ሥርዓት ቃል ኪዳን

PDF    የፖለቲካ ፓርቲዎች የቃል ኪዳን ሰነድ ለማስፈጸም የወጣ የሥነ ሥርዓት ደንብ

PDF    በተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚደረገው ውይይት የሚመራበት ሥርዓት እና ደንብ

PDF    ለዕጩዎች የተዘጋጀ ምልክት

5. ሕጎች  

PDFየሥራ አመራር ቦርድ የስብሰባ ሥነ ሥርዓት መመሪያ ቁ. 1 2013

PDFየክልል ጽቤት ኃላፊዎች ምልመላ መመሪያ ቁ.1 2011 ዓ.ም

PDFየመገናኛ ብዙሃን እና የጋዜጠኞች የምርጫ አዘጋገብ የስነ ምግባር እና አሰራር መመሪያ ቁጥር 02 2013

PDFበኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ተመዝግበው የሚገኙ የአገር አቀፍና የክልል ፓርቲዎች (በአዋጅ ቁ. 1162 2011 መሰረት) ማሟላት ያለባቸውን ግዴታዎች ለማስፈፀም የወጣ መመርያ ቁ 3 2012 

PDFየመራጮች ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ እና ስነ-ምግባር መመሪያ ቁጥር 4 2012

PDFየሀገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች ፈቃድ አሰጣጥ፣ አሠራር እና ስነ ምግባር መመሪያ ቁጥር 5 2012 ዓ.ም

PDFየመራጮች ምዝገባ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 6 2013 ዓ.ም.

PDFየእጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ፣ የድጋፍ ፊርማ አሰባሰብ እና መለያ ምልክት አመራረጥ መመሪያ ቁጥር 7 2013

PDFየምርጫ ማስፈጸሚያ ቁሳቁሶችና እና ሰነዶች ድልድል፣ ሥርጭት፣ አጠቃቀም፣ ርክክብና አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 8 2013

PDFበምርጫ ወቅት የኮቪድ- 19 ስርጭትን ለመቀነስ የወጣ መመሪያ ቁጥር 9/2013

PDFበምርጫ ሂደት በየደረጃው ስለሚኖር ቅሬታ አቀራረብ፣ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አደረጃጀት እና አሰራር መመሪያ ቁጥር 10 2013

PDFየውጪ የምርጫ ታዛቢዎች ፍቃድ አሰጣጥ፣ የአሠራር ሥርዓት እና የሥነ ምግባር መመሪያ ቁጥር 11/2013

PDFበምርጫ ማስፈጸሚያ አደረጃጀቶችና በምርጫ ተግባራት ላይ ሰላምና ጸጥታ የሚያስከብሩ የጸጥታ አስከባሪ አካላት የአሠራር ሥርዓት እና የሥነ-ምግባር መመሪያ ቁጥር 12 2013

PDFበልዩ ሁኔታ የሚቋቋሙ የምርጫ ጣቢያዎች መመሪያ ቁጥር 13/2013

PDFየድምፅ አሰጣጥ፣ ቆጠራና ውጤት አገላለፅ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 14 2013 ዓ.ም.

PDFየድጋሚ ምርጫ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 15 2013 ዓ.ም

PDFመንግሥት ለፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 16/2013

PDFየእጩ ተወዳዳሪዎች ወኪሎች የፍቃድ አሰጣጥ፣ የአሰራር እና የሥነ-ምግባር መመሪያ ቁጥር 17/2013 ዓ.ም

PDFመመሪያ ቁጥር 19/2015 ዓ.ም

PDF የፖለቲካ ፓርቲዎችና የምርጫ ሂደት አቤቱታዎች አጣሪ ጉባዔ መመሪያ ቁጥር 21/ 2015

PDFየምክር ቤት አባላት በመራጮቻቸው አመኔታ በሚያጡበት ጊዜ ስለሚወሰድ እርምጃ ዝርዝር የአሰራር ስርዓት ለመደንገግ የወጣ መመሪያ ቁጥር 22/2016 ዓ.ም

PDFበልዩ ምርጫ ክልሎች የመራጮች ምዝገባ አተገባበር ማዕቀፍ

PDFበፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚደረግ ውይይት መመሪያ
PDFየድምፅ መስጫ ወረቀቶች አወጋገድ ሂደት ሰነድ