Skip to main content

የተሳሳተ ዜና ጥቆማ

መስከረም 27 ቀን 2012 ዓ.ም.

ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2012 ዓ.ም. “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የፓለቲካ ፓርቲዎች ሊያደርጉት የነበረው ውይይት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ” በሚል ርእስ በኢትዮጵያ ብርድካስቲንግ ኮርፓሬሽን ፌስቡክ ገጽ የተዘገበው ዜና የተሳሳተ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለማሳወቅ ይወዳል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬ ዕለት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ያደረገው ምንም ዓይነት ውይይትም ሆነ ድርድር ያላደረገ ሲሆን የኢቢሲም ሆነ የኢቢሲን ዜና መሠረት በማድረግ የዘገቡ ሌሎች ሚዲያዎች ዜናዎችን ከማሰራጨታቸው በፊት ማጣራት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያሳስባል። ቦርዱ ማንኛውንም የመረጃ ጥያቄዎች ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ ይወዳል።

Share this post

የምርጫ ክልል ሃላፊነት ስራ ምደባ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ9ኙ ክልሎችና ለ2ቱ ከተማ አስተዳደሮች የምርጫ ክልል ሃላፊነት አወዳድሮ ለመመደብ የስራ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ ነገር ግን ለሃረሪ ክልል፣ ለድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር፣ ለጋምቤላ ክልል፣ ለአማራ ክልል በቂ አመልካች ባለመገኘቱ ከስር የተጠቀሰውን ዝርዝር መስፈርት የምታሟሉ እና በሶስቱ ክልሎች እና በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር መስራት ለምትፈልጉ የማመልከቻ ጊዜው ከዛሬ ከመስከረም 26 2012 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት ስለተራዘመ ማመልከቻችሁን ማስገባት እንደምትችሉ ያሳውቃል፡፡

የሲዳማ ክልልነት ህዝበ ውሳኔ አፈጻጸም መርሃ ግብር ለውጥ

የሲዳማ ክልልነት ህዝበ ውሳኔ አፈጻጸም መርሃ-ግብር መሰረት የቅስቀሳ ጊዜ ከመስከረም 23 - 28 ቀን 2012 ዓ.ም በሚል ታቅዶ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ነገር ግን የህዝበ ውሳኔ ቅስቀሳው የመራጮች ምዝገባ ከሚደረግበት ጊዜ ጋር የተቀራረበ ቢሆን ይሻላል በሚል ስለታመነበት የቅስቀሳ መርሃግብሩ ከጥቅምት 18 - 22 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት እንዲሆን ተብሎ ተሻሽሏል፡፡ ቦርዱ በአፈጻጸም ጉዳዮች የተነሳ የሚኖሩ የቀናት ለውጥና መሸጋሸጎችን ለወደፊትም ይፋ የሚያደርግ ይሆናል፡፡


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የተዛባ መረጃ ማስተካከያ

መስከረም 14 ቀን 2012 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኢዜማ ፓርቲ መሪ እውነታ አዛብቶ የሚያቀርብ ንግግር ላይ ማስተካከያ የሰጠ ሲሆን ወደፊትም በተመሳሳይ ክትትል በማድረግ የተዛቡ መረጃዎችን እርምት እንደሚሰጥ ለመግለጽ ይወዳል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማስታወሻ የኢዜማ ፓርቲ መሪ ንግግር ከስር በሚገኘው ማስፈንጠሪያ ከ4ተኛ ደቂቃ ጀምሮ ይገኛል።

Ethiopia -ESAT Bezih Samint ከፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር በወቅታዊ የሀገራችን ጉዳይ ላይ

 

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊዎች ምልመላ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዋና መስሪያ ቤት ደረጃ የጀመረውን ውስጣዊ አደረጃጀት ሪፎርም በክልል ደረጃ በማስፋት በ9 ክልሎች የሚገኙት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶቹን እንደአዲስ እያደራጀ ይገኛል፡፡ የዚህ ስራ ዋናው አካል የክልል የምርጫ ሃላፊዎችን እንደስራ አመራር ቦርዱ አባላት አመራረጥ ሁሉ የሚመለከታቸው አካላት የተሳተፉበት እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ በዚህም መሰረት በዘጠኙ ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች በእጩነት ለመወዳደር የሚፈልጉና ከስር የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ግለሰቦች የአመላመል ሂደት እንዲሁም በመጨረሻ ይህን የክልል ቅርጫፍ መስሪያ ቤት ዋና ሃላፊነትን አስመልከቶ ቦርዱ የሚሰጠው የቅጥር ውሳኔ በሚዲያ በይፋ የተገለጸ እንዲሆን ማድረግ አስፈልጓል፡፡

በዚህም መሰረት በክልል የምርጫ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊነት በዕጩነት የሚቀርቡ አመልካቾች ማሟላት የሚኖርባቸው መስፈርቶች፡-

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ዞን ሕዝበ ውሳኔን አፈጻጸም አስመልክቶ ከክልልና ዞን ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ

ጳጉሜ 2 ቀን 2011 ዓ.ም.       

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ዞን ሕዝበ ውሳኔን አፈጻጸም አስመልክቶ የተለያዩ አካላት ጋር የሚደረጉ የተለያዩ ውይይቶችን እንደሚያከናውን ባስቀመጠው የድርጊት መርሃ ግብር መሠረት ነሐሴ 30 ቀን 2019 ዓ.ም. ከደቡብ ክልል ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ምክር ቤት ተወካዮች፣ የክልሉ አመራር አባላትና ከዞኑ ተወካዮች ጋር ውይይት አካሒዷል፡፡ በውይይቱ ላይ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች አፈጉባኤ ሄለን ደበበ፣ ምክትል አፈጉባኤ መንግሥቱ ሻንካ፣ የክልል መስተዳደር ጽ/ቤት ዋና አማካሪ አኒሳ መልኮ፣ የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደስታ ሌዳሞ፣ ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጥራቱ በየነ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ከቦርዱ አባላት ጋር ገንቢ ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱም ላይ፦

Share this post

የሚዲያዎች ዘገባ ማስተካከያ

ሐምሌ 18 ቀን 2011 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያለበትን ከፍተኛ የሥራ ጫና፣ የአቅም ውስነንነት እና የሪፎርም ሥራ መደራረብ የተነሳ በዚህ ዓመት መደረግ የነበረበትን የአካባቢ ምርጫ እና የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ ምክር ቤቶች ምርጫ ማካሄድ እንደማይችል ለኢፌዴሪ ተወካዮች ምክር ቤት በጽሁፍ የገለጸ ቢሆንም ምርጫዎቹ ከሚቀጥለው አገራዊ ምርጫዎች ጋር እንዲካሄዱ ምክረሃሳብ ያቀረበውም ሆነ ውሳኔ ያሳለፈው የተወካዮች ምክር ቤት ነው። በመሆኑም ቦርዱ የአካባቢ ምርጫም ሆነ የሁለቱ ከተማ ምክር ቤቶች ምርጫ ከአጠቃላይ ምርጫ ጋር መካሄድ አለባቸው የሚል የውሳኔ ሀሳብ አቅርቧል የሚለው የሚዲያዎች ሪፓርት ማስተካከያ እንዲደረግበት እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Share this post

ባለሞያዎች ዝርዝር ውስጥ ማካተቻ ጥሪ

ይህ የስራ ማስታወቂያ አይደለም፡፡
ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተላለፈ ለባለሞያዎች ዝርዝር(Professionals roster) ውስጥ ማካተቻ ጥሪ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባለፉት ስድስት ወራት የተለያዩ ተቋማዊ ለውጦችን ለማካሄድ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ከነዚህም ለውጦች መካከል ዋናው ተቋሙን ከፍተኛ አቅምና ቁርጠኝነት ያለው የሰው ሃይል እንዲኖረው ጥረት ማድረግ ነው፡፡
በዚህም መሰረት የቦርዱ ጽ/ቤት በተለያዩ ሞያዎች የከፍተኛ ክህሎት ባለቤት የሆኑ ግለሰቦችን ግለታሪክ (ካሪኩለም ቪቴ) መሰብሰብና የባለሞያዎች ዝርዝር በማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖም ሲገኝ በበጎ ፍቃደኝነት፣ በጊዜያዊ ኮንትራት ስራ፣ እንዲሁም በቅጥር ከተቋሙ ጋር አብረው መስራት የሚችሉበትን መንገድ ለማመቻቸት ይፈልጋል::

በአዲሱ የምርጫና የፓለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ላይ የተደረገው ውይይት

ሐምሌ 24 ቀን 2011 ዓ.ም.        

በአዲሱ የምርጫና እና የፓለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ላይ የተደረገውን ውይይት አስመልክቶ የፋና ብሮድካስቲንግ ዘገባን ማየት ይችላሉ። ዘገባው የተነሱ ጥያቄዎችንና በቦርዱ ኃላፊዎችና በህግ አርቃቂ ባለሞያዎች የተሰጡትን መልሶች ያስቃኛል።

http://bit.ly/2Q2EYSq 

 

Share this post