Skip to main content

ባለሞያዎች ዝርዝር ውስጥ ማካተቻ ጥሪ

ይህ የስራ ማስታወቂያ አይደለም፡፡
ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተላለፈ ለባለሞያዎች ዝርዝር(Professionals roster) ውስጥ ማካተቻ ጥሪ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባለፉት ስድስት ወራት የተለያዩ ተቋማዊ ለውጦችን ለማካሄድ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ከነዚህም ለውጦች መካከል ዋናው ተቋሙን ከፍተኛ አቅምና ቁርጠኝነት ያለው የሰው ሃይል እንዲኖረው ጥረት ማድረግ ነው፡፡
በዚህም መሰረት የቦርዱ ጽ/ቤት በተለያዩ ሞያዎች የከፍተኛ ክህሎት ባለቤት የሆኑ ግለሰቦችን ግለታሪክ (ካሪኩለም ቪቴ) መሰብሰብና የባለሞያዎች ዝርዝር በማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖም ሲገኝ በበጎ ፍቃደኝነት፣ በጊዜያዊ ኮንትራት ስራ፣ እንዲሁም በቅጥር ከተቋሙ ጋር አብረው መስራት የሚችሉበትን መንገድ ለማመቻቸት ይፈልጋል::

በአዲሱ የምርጫና የፓለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ላይ የተደረገው ውይይት

ሐምሌ 24 ቀን 2011 ዓ.ም.        

በአዲሱ የምርጫና እና የፓለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ላይ የተደረገውን ውይይት አስመልክቶ የፋና ብሮድካስቲንግ ዘገባን ማየት ይችላሉ። ዘገባው የተነሱ ጥያቄዎችንና በቦርዱ ኃላፊዎችና በህግ አርቃቂ ባለሞያዎች የተሰጡትን መልሶች ያስቃኛል።

http://bit.ly/2Q2EYSq 

 

Share this post

በአዲሱ የምርጫና እና የፓለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ላይ ሕዝባዊ ውይይት ተደረገ

ሐምሌ 18 ቀን 2011 ዓ.ም.

በጠቅላይ አቃቤ ህግ ስር በሚገኘው በህግና በፍትህ ማሻሻያ ምክር ቤት የዴሞክራሲ ተቋማት የሥራ ቡድን አዲሱ የምርጫና የፓለቲካ ፓርቲዎች አዋጅን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበርና ከተለያዩ የፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመወያየት የተረቀቀውን ህግ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ በትላንትናው ዕለት የዴሞክራሲና የፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለሕዝብ ክፍት የሆነ ውይይት ያዘጋጀ ሲሆን የተለያዩ የፓለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች ተሳትፈውበታል፡፡ በዚህ ውይይት የተለያዩ በህጉ ላይ የተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ የተሰጠባቸው ሲሆን ሁለት ጉዳዮች በዋናነት ሰፊ ውይይትና ክርክር ተደርጎባቸዋል፡፡ የህግ አርቃቂ ባለሞያዎቹ እና የቦርዱ ኃላፊዎችም ለጥያቄዎቹ መልስ የሰጡ ሲሆን የህጉን መነሻ መርሆዎች በዝርዝር ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡

ሁለቱ ከፍተኛ ክርክር የተደረገባቸው ጉዳዮች;

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ከጣልያንዋ ምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል

ሰኔ 13 ቀን 2011 ዓ.ም.   

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ከጣልያንዋ ምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል በውይይቱም ወቅት የሚቀጥለውን ምርጫ አስመልክቶ በጣልያን መንግሥት እና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መካከል ሊኖር ስለሚችለው ትብብር ተነጋግረዋል። ሚኒስትሯ በበኩላቸው የጣልያን መንግሥት የሚቀጥለውን ምርጫ ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለመደገፍ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል።

Share this post

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በትላንትናው ዕለት ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት እና ከገንዘብ ሚኒስትር ጋር በመሆን የጋራ የፕሮጄክት ሰነድ ፈርመዋል

ሰኔ 13 ቀን 2011 ዓ.ም.        

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በትላንትናው ዕለት ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት እና ከገንዘብ ሚኒስትር ጋር በመሆን የጋራ የፕሮጄክት ሰነድ ፈርመዋል። የ40 ሚልዮን ዶላር በጀት ያለው የፕሮጄክት ሰነዱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚቀጥለውን አገራዊ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሃዊና ተአማኒ እንዲሆን የምርጫ ቦርድን አቅም ማሳደግን ጨምሮ ለተለያዩ ከምርጫ ጋር ግንኙነት ላላቸው ተግበራት መሳካት የሚውል ሲሆን ካናዳ፣ ዴንማርክ፣ ፊንላንድ፣ ጀርመን፣ አየርላንድ፣ ጃፓን፣ ኔዘርላንድ፣ ኒውዚላድ፣ ኖርዌይ እና ስዊድን ለበጀቱ አስተዋእጾ አድርገዋል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባላትን ለመሾም በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አማካኝነት የተቋቋመው እጩዎችን መልማይ ኮሚቴ በዛሬው እለት ስምንት እጩዎችን ይፋ አድርጓል፡፡

ሰኔ 1 ቀን 2011 ዓ.ም.                                                                                                                                                                                                       

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባላትን ለመሾም በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አማካኝነት የተቋቋመው እጩዎችን መልማይ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ስምንት እጩዎችን ይፋ አድርጓል። ስምንቱ እጩዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመጨረሻ ውሳኔ የቀረቡ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሚቀጥሉት ሳምንታት አራቱን የቦርድ አባላት ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው ያፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

http://bit.ly/3380LwZ   

Share this post

ቦርዱ ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጋር ምክክር አካሄደ

ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የሚዲያዎች ሚና” በሚል ርዕስ ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጋር ምክክር አደረገ። ቦርዱ ከአውሮፓ ህብረት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የምክክር አውደጥናት ግንቦት 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ተካሂዷል፡፡

Share this post