ጥያቄ - ኮቪድ19 እና ምርጫው ላይ የሚኖረውን ተጽእኖ አስመልክቶ የፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር አልተደረገም ነበር?
መልስ - ቦርዱ የኮቪድ19 በምርጫ ላይ የሚኖረውን ተጽእኖ አስመልክቶ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር አድርጓል፡፡ ያደረገው ምክክር በሁለት ዙር ሲሆን በእለቱም ፓለቲካ ፓርቲዎች የተለያዩ አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡ የሰጧቸው አስተያየቶችም ችግሩን አለም አቀፍነት በተለይ ደሞ እንደኢትዮጵያ ላለ አገር ሊያስክተል የሚችለውን ቀውስ እና በምርጫ ስራ ላይ የሚያመጣውን ተጽእኖ እንደሚረዱ ገልጸዋል፤ ምርጫ ቦርዱ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመመካከር እንዲሰራም ጠይቀዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ቦርዱ ምክክሩን ማድረጉን አድንቀው መንግስት ያስቀመጠው የ14 ቀን ክልከላ ታይቶ ቢወሰን የሚል አማራጭም አቅርበዋል፡፡ ውይይቱ በመግባባት የተጠናቀቀ ሲሆን የፓርቲ አመራሮች ይህንን እድል የአገራችንን ፓለቲካ ለማስተካከልም ሆነ በቂ ዝግጅት ለማድረግ መጠቀም እንደሚገባ፣ ይህ ውሳኔ በቦርዱ መወሰን እንዳለበት እና ፓርቲዎችን ማማከር ጥሩ ቢሆንም ውሳኔው ከፓርቲዎች በላይ መሆኑን እና በአገር የመጣ ከአቅም በላ