Skip to main content

የጨረታ ማስታዎቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛውን አጠቃላይ ምርጫ ተከትሎ የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ እና የምርጫ ጣቢያዎችን ተደራሽነት የሚፈትሽ የዳሰሳ ጥናት እንዲሰሩ አማካሪ ድርጅቶችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁ አማካሪ ድርጅቶች እና ባለሞያዎች እስከ ጥር 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ በምርጫ ቦርድ ዋናው ቢሮ ግዢ ክፍል ቢሮ ቁጥር 107 በመምጣት የጨረታ ሰነዳችሁን ማስገባት ትችላላችሁ፡፡

ስለሥራው ዝርዝር መረጃ ከስር ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

እዚህ ላይ ይጫኑ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከ UNDP (United Nations Development Programme)ጋር በመተባበር በ BRIDGE (Building Resources in Democracy, Governance and Elections) አማካሪዎች አማካኝነት ለምርጫ ቦርድ የበላይ አመራሮች እና ኃላፊዎች ሥልጠና ሰጠ

ሥልጠናው “የምርጫ ተቋማዊ ልህቀት ግንባታ” (Building Institutional Excellence in Elections) በሚል ርዕስ የተሰጠ ሲሆን የቦርድ አባላት፤ የጽ/ቤት ኃላፊዎች፤ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች እና ከቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተውጣጡ በድምሩ 25 የሚሆኑ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈውበታል፡፡

ሥልጠናው በዋናነት የምርጫ አስተዳደርን፣ መዋቅራዊ አደረጃጀትን፣ ዕቅድን፤ የድርጅት ባህልን፤የውስጥ እና የውጭ ተግባቦትን፤አጋርነትን እና ስኬታማ የአመራር ሂደትን በተመለከቱ ሃሳቦችን ዙሪያ ያተኮረ ነበር፡፡

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጄንሲ አብረው ለመሥራት የሚያስችላቸው የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረሙ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መራጮች በቂ የሆነ የሥነ-ዜጋ እና የምርጫ ነክ ግንዛቤ የሚያገኙበትን ስልት በመቀየስና የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም የሥነ-ዜጋና የመራጮች ትምህርት መስጠት ከዋና ዋና ተግባራቱ መካከል አንዱ ነው፡፡ ቦርዱ የሥነ-ዜጋና የመራጮች ትምህርትን በቋሚነት ተደራሽ ለማድረግ ይረዳው ዘንድ የተለያዩ የህትመት ውጤቶችን በማዘጋጀት በትምህርት ተቋማት፣ በህዝብ ቤተ-መጻሕፍት፣ በመንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ውስጥ በማስቀመጥ ለዜጎች ተደራሽ በማድረግ ላይ ይገኛል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቦርዱ የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትል እና ግምገማ ላይ ያተኮረ ሥልጠና እየሠጠ ይገኛል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቦርዱ የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትል እና ግምገማ የሥራ ክፍል አስተባባሪነት 45 ለሚሆኑ የቦርዱ የክልል ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የዲፓርትመንት ኃላፊዎች እና ኤክስፐርቶች በዕቅድ ዝግጅት (Planning)፣በጀት አያያዝ (Budgeting)፣ ክትትል እና ግምገማ (Monitoring and Evaluation)፣ የአፈጻጸም ሪፖርት አዘገጃጀት (Reporting)፤የሠራተኛ ምዘና (Performance Evaluation and Coach for Performance) ላይ ያተኮረ ሥልጠና እየሠጠ ይገኛል፡፡

ከታህሣሥ 22 እስከ ታህሣሥ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ የሚቆየው ሥልጠና ዋና ዓላማ እያንዳንዱ ኃላፊ የሥራ ክፍሉን ተግባራት ለማቀድ፤በጀት ለመመደብ እና ደረጃውን የጠበቀ ሪፖርት ለማቅረብ የሚያስችለውን ዕዉቀት እና ክህሎት ለማስጨበጥ ያለመ ነው፡፡

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተለያዩ የሕትመት ውጤቶችን በማዘጋጀት በትምህርት ተቋማት፣በህዝብ ቤተ- መጻሕፍት፣ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ውስጥ በማስቀመጥ ለዜጎች ተደራሽ እያደረገ ይገኛል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሕግ ከተሰጡት ኃላፊነቶች መሀከል መራጮች በቂ የምርጫ ነክ ግንዛቤ የሚያገኙበትን ስልት መቀየስና በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም የሥነ ዜጋና የመራጮች ትምህርትን መስጠት አንዱ ነው፡፡ በዚህም መሠረት የሥነ ዜጋና የመራጮች ትምህርትን በቋሚነት ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ የሕትመት ውጤቶችን በማዘጋጀት በትምህርት ተቋማት፣በህዝብ ቤተ- መጻሕፍት፣ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ውስጥ በማስቀመጥ ለዜጎች ተደራሽ እያደረገ ይገኛል።

Share this post

ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ

ከዚህ ቀደም ቦርዱን በሰብሳቢነት ሲመሩ የነበሩት ብርቱካን ሚደቅሳ ከነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በገዛ ፈቃዳቸው ሥራቸውን መልቀቃቸው ተከትሎ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ ሾሟል፡፡

ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ ቀደም ብሎም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመሆን ከየካቲት 2012 ዓ.ም እስከ የካቲት 2015 ዓ.ም ማገልገላቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከወዲሁ ለወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው ይመኛል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ታህሣሥ 9 ቀን 2016 ዓ.ም.

Share this post

በስነ ዜጋ እና መራጮች ትምህርት ላይ ለሚሳተፉ የሲቪል ማህበራት የቀረበ ጥሪ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሕገ መንግስቱ እና በአዋጅ ቁጥር 1133/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሰረት የመራጮች ትምህርት ለሚሰጡ የሲቪል ማህበራት ፍቃድ ይሰጣል።

የስነ ዜጋ እና የመራጮች ትምህርት አስፈላጊነት ዜጎች በምርጫ ለመሳተፍ እና ተዓማኒነት ያለው ምርጫ ለማድረግ በሚወስኑት ውሳኔ ላይ ተፅዕኖው በግልፅ ይታያል፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃም ይህንን ግብ እውን ለማድረግ የሲቪል ማህበረሰብ ተሳትፎም አስፈላጊ ነው።

በስነዜጋ እና በዲሞክራሲያዊ ምርጫ እሳቤዎች ዙርያ የክርክር መድረኮችን ለማዘጋጀት ፍላጎት ላላቸው ተቋማት የቀረበ ጥሪ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተማሪዎች እና ወጣቶች መካከል በስነዜጋ እና በዲሞክራሲያዊ ምርጫ እሳቤዎች ዙርያ የክርክር መድረኮችን ለማዘጋጀ ፍላጎት ላላቸው ተቋማት ጥሪ ያቀርባል።

በመሆኑም ከዚህ በፊት ጥያቄ/ ማብራሪያ ያስገባችሁም ሆነ በዚሁ ጉዳይ ላይ ፍላጎት ያላችሁ መንግስታዊ ያልሆናችሁ ተቋማት እና ሚዲያዎች በተናጠል ወይም በጋራ የምርጫ ክርክር ዝርዝር የፍላጎት መግለጫ ወረቀት (Expression of interest) ለቦርዱ እንድታቀርቡ ጥሪ ያቀርባል።

ማንኛውም ክርክር ለማከናወን የሚያስብ ተቋም የሚመለከቱትን ዋና ዋና ነገሮችን ያሟላ የፍላጎት መግለጫ ሊያቀርብ ይገባል።