Skip to main content

ድጋሚ የወጣ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛው ዙር የጠቅላላ ምርጫ በተለያዩ ምክንያቶች ባልተካሄደባቸው የምርጫ ክልሎች ምርጫውን ለማከናወን በዝግጅት ላይ ይገኛል።

በዚህም መሰረት በአፋር ክልል በ ዞን 5 በሚገኙ ወረዳዎች በሙሉ ፣ በቡሬሞዳይቱ ፣ ገዋኔ ፤ በዳሎል እና በጉሊና የምርጫ ክልሎች ላይ እንዲሁም በቤንሻንጉል ጉምዝ በአሶሳ ዞን አሶሳ ሆሃ፣ አሶሳ መገሌ፣ መንጌ እና ኦዳብልድጉል በካማሺ እና መተከል ዞኖች ሁሉም ወረዳዎች በሶማሌ ክልል ጅጅጋ ከተማ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስቃን ማረቆ 2 ላይ ነዋሪ የሆኑ እና መስፈርቱን የሚያሟሉ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎችን ቦርዱ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል በዚህም መሰረት፤

• ከ 18 አመት በላይ የሆናችሁ

• ከዚህ በፊት በምርጫ አስፈጻሚነት ያገለገላችሁ

• የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆናችሁ

• የ 12ተኛ ክፍል እና ከዛ በላይ የትምህርት ዝግጀት ያላችሁ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከታዛቢ ሲቪል ማኅበራት እና የሰብአዊ መብቶች ተከታታይ ድርጅቶች ጋር በተያዘው ዓመት የሚካሄደው ምርጫን አስመልክቶ ውይይት አካሄደ

የኢትዮጵ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቤንሻንጉል ጉምዝ፣ በአፋር፣ በሶማሌና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ላይ ለሚያከናውነው የ6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ቀሪና የድጋሚ ምርጫን አስመልክቶ ጊዜያዊ የጊዜ ሠሌዳ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። ይኽንንም ተከትሎ ቦርዱ የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ከታዛቢ ሲቪል ማኅበራት እና የሰብአዊ መብቶች ተከታታይ ድርጅቶች ጋር ውይይት አካሂዷል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት በተከናወነው የታላቁ ሩጫ ፕሮግራም ማስተዋወቂያ ላይ በመገኘት ለታዳጊ ተማሪዎች ስለምርጫ ምንነትና የድምጽ አሰጣጥ ሂደት በተግባር የተደገፈ የግንዛቤ ማስጨበጫ ገለፃ አደረገ፡፡

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሴቶች እና የአካል ጉዳተኞች ሩጫ አስተባባሪዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ለመነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት ፕሮግራሙን አስተዋውቋል፡፡ በዚህ መርሀ ግብር ላይ የተጋበዘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በተለይም ለታዳጊ ተማሪዎች ስለምርጫ ምንነት እና በኢትዮጵያ የምርጫ ሂደት ዙሪያ በተግባር የተደገፈ የግንዛቤ ማስጨበጫ ገለፃ አድርጓል፡፡

Share this post

በስነ ዜጋ እና መራጮች ትምህርት ላይ ለሚሳተፉ የሲቪል ማህበራት የቀረበ ጥሪ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1133/2011 እና የኢትዮጵያ ምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና በመራጮች ትምህርት እውቅና አሰጣጥ እና ስነ ምግባር መመሪያ ቁጥር 4/2020 በተደነገገው መሰረት በህጋዊ መንገድ የተመዘገቡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችንና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን የመራጮች ትምህርት መስጠት እንዲችሉ እውቅና የመስጠት ኃላፊነት አለበት።

Share this post

ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. እንዲሁም መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ማካሄዱ ይታወቃል። ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች ምርጫው ባልተካሄደባቸው በ አፋር፤ ቤንሻንጉል ጉምዝ በሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ2016 ዓ.ም. በጀት ምርጫውን ለማከናወን በዝግጅት ላይ ይገኛል። በዚህም መሰረት በ አፋር ክልል (በ ዞን 5 በሚገኙ ወረዳዎች በሙሉ ፣በ ዞን 3 ቡሬሞዳይቱ እና ገዋኔ፤ በዞን 2 ዳሎል እንዲሁም በዞን 4 ጉሊና) የምርጫ ክልሎች ላይ እንዲሁም በ ቤንሻንጉልጉምዝ በአሶሳ ዞን አሶሳ ሆሃ፣ አሶሳ መገሌ፣ መንጌ እና ኦዳብልድጉል፤ በካማሺ እና መተከል ዞኖች ሁሉም ወረዳዎች በሶማሌ ክልል ጅጅጋ ከተማ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስቃን ማረቆ 2 ላይ መስፈርቱን የሚያሟሉ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎችን ቦርዱ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል በዚህም መሰረት፤

•ከ 18 አመት በላይ የሆናችሁ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4/12 ምክር ቤት ጋር በመተባበር በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና በምርጫ ሂደት ዙሪያ ሥልጠና ሰጠ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4/12 ምክር ቤት በተደረገለት ግብዣ መሰረት የስነ-ዜጋና መራጮች ትምህርት ክፍል ከቦርዱ አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት እንዲሁም ከምርጫ ኦፐሬሽንስ የሥራ ክፍል ጋር በመቀናጀት ለሕፃናት ፓርላማ አባላትና ለባለድርሻ አካላት በዲሞክራሲያዊ ምርጫ የዜጎች መብትና ሃላፊነቶች፥ የኢትዮጵያ የምርጫ ሂደትን ከምርጫ ህጉ አኳያ እና በሕፃናት የፓርላማ አሰራር፥ አወቃቀርና መልሶ ማደራጀት ዙሪያ ላይ ያተኮረ የአንድ ቀን ሥልጠና የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ሰጥቷል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ኮንግረስ ፓርቲ ከሀገር ዓቀፍ የፖለቲካ ፓርቲነት እንዲሰረዝ የኢትጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የወሰነውን ውሳኔ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመቀበል የሰጠው ውሳኔ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ኮንግረስ በአዋጅ ቁጥር 1162/11 መሰረት በሀገር ዓቀፍ ፓርቲነት ለመመዝገብ ጥያቄ አቅርቦ በአዋጁ አንቀጽ 64 መሰረት ፓርቲው ከአምስት ክልሎች ማቅረብ የሚገባውን አስር ሺህ (10,000) የመስራች አባላት በቁጥር ያቀረበ ቢሆንም የክልላዊ አባላት ስብጥርን በሚመለከት ግን ከአንድ ክልል መሟላት ከሚገባው አንድ ሺህ አምስት መቶ (1,500) መስራች አባላት ውስጥ አንድ ሺህ አርባ አምስት (1,045) መስራች አባላት ብቻ ያቀረበ በመሆኑ ለሀገር ዓቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ የሚያስፈልገውን የመስራች አባላት ክልላዊ ስብጥር አሟልቶ ስላልቀረበ ከየካቲት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ከፖለቲካ ፓርቲነት እንዲሰረዝ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ወስኖ ነበር፡፡

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በስነ-ዜጋ እና የመራጮች ትምህርት ላይ በትኩረት እየሠራ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በስነ-ዜጋ እና መራጮች ትምህርት ላይ በትኩረት እየሠራ ሲሆን ዜጎች በቂ የስነ-ዜጋ እና ምርጫ ነክ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ቦርዱ የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ትምህርት እየሰጠ ይገኛል። በዚሁ መሠረት የስነ-ዜጋ እና መራጮች ትምህርት የሥራ ክፍል ከቦርዱ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና የህዝብ ቤተ-መጻሕፍት አስተማሪ የሆኑ የተለያዩ የሕትመት ውጤቶችን ማለትም ቡክሌት እና ብሮሸሮችን የግንዛቤ ገለፃ በመስጠት ማሰራጨት ተችሏል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የስነ-ዜጋ እና መራጮች ትምህርት ለሚሰጡ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ስልጠና እና የእውቅና ምስክር ወረቀት ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የስነ-ዜጋና መራጮች ትምህርት የሥራ ክፍል በምርጫና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከሚሠሩ 40 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር ከ ጥር 29 እስከ ጥር 30 ቀን 2016ዓ.ም. ድረስ ለሁለት ቀናት የቆየ የስልጠና መድረክ አዘጋጀ። መድረኩ በምርጫ ቦርድ አመራር አባል ዶ/ር አበራ ደገፋ የመክፈቻ ንግግር የተከፈተ ሲሆን በመክፈቻ ንግግራቸው የስነ-ዜጋና መራጮች ትምህርትን በቋሚነት የመስጠትን ጠቀሜታ ካብራሩ በኋላ ይህ እንዲሳካ ከቦርዱ ባልተናነሰ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ዋነኛ ሚና እንደሚጫወቱ አብራርተዋል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ የምርጫ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ዓ.ም. በተሰጠው ሥልጣን መሠረት፣ ለሶስት የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባና የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሰጠ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ የምርጫ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ዓ.ም. በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ‘የወሎ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ’ ተብሎ ለሚጠራ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ፤‘የኩሽ ህዝቦች ብሔራዊ ንቅናቄ’ ተብሎ ለሚጠራ ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ እና ‘ብሔራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ’ ለተባለ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ጥር 21 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባና የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሰጠ፡፡

Share this post