የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሥሩ ለሚገኙ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች ተለማማጅ ሰራተኞችን /Internship/ ቀጥሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚሁም መሠረት ከዚህ በታቸው የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተጠቀሰው የስራ ማመልከቻ ማስፈንጠሪያ በመንካት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  • በማኔጅመንት/ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን/ በአካውንቲንግና ፋይናንስ/ በኢኮኖሚክስ/ በማርኬቲንግ/ በሕግ/ በኮምፒውተር ሳይንስ/ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ወይም በሌላ ተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪና 0 ዓመት የሥራ ልምድ
  • በቂ የመግባባት ችሎታ ያላት/ያለው
  • የተቋሙን ደንብና መመሪያ የምታከብር/ የሚያከብር
  • ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነች/ያልሆነ፤
  • የቅጥር ሁኔታ፡ በጊዜያዊነት
  • የስራ ቦታ አዲስ አበባ፣ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ሶማሌ እና ቤኒሻጉል
  • አመልካቾች ከዚህ በታች በተቀመጠው የድርጅቱ ድህረገፅ ላይ መመልከት ይችላሉ፡፡

እዚህ ላይ ይጫኑ

ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ።

ማሳሰቢያ፡-

ለሶማሌ ክልል ላይ አመልካቾች የክልሉን ቋንቋ ማወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የስራ ማስታወቂያ
ሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም